የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ግ.ጨ
ከ/ስ/ፋ/03/2012/13
የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የስኳር ማሽጊያ ከረጢት (PP ag)
- ሎት 2- የፋብሪካ ኬሚካል
- ሎት 3- የተሽከርካሪ ጎማና ከለመንዳሪ
- ሎት 4 – ቆንጨራ እና ሞረድ ናቸው፡፡
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN no) ፤ የወቅቱን የታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ለእያንዳንዱ ሎት 1. 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ሎት 2፣ 3 እና 4 ለእያንዳንዳቸው 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ ኦርጅናል ሠነድ ጋር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ መስከረም 29/2013 ዓ.ም በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የመዝጊያ ሰዓት ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም ዕቃ ስለእቃው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡– ከሰም ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ካዛንቺስ ከመነኸሪያ ሆቴል ወደ አቧሬ በሚወስደው መንገድ ከጨርጨር ሥጋ ቤት 100ሜ ዝቅ ብሎ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011-878-71-98 ወይንም 011-878-71-84 ይደውሉ
ከሰም ስኳር ፋብሪካ