የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ 008/2012
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት በዞኑ ም/ቤት በኩል
- የዞኑ ም/ቤት አዳራሽ ጥገናና ማስፋፊያ ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም :-
- ደረጃቸው GC-7/BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- የዘመኑን ፈቃድ ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- ተጫራቾች 15,000.00 /አሥራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ዋስትና በሲፒኦ /የባንክ ጋራንት/ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከዞኑ ውስጥ በሚሠሩ ግንባታዎች ውል ያቋረጡ ኮንትራክተሮች መወዳደር አይችሉም።
- ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥ ተወዳድረው አሸንፈውና ውል ገብተው እየሠሩ ያሉ ከሆነ ሥራቸው ከ70% በላይ መድረሱን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ካልሆነ በጨረታው መወዳደር አይችሉም ::
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር ከሥራ ቀናት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማሸግና አንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 9:00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታ ው በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወሎቻቸው በተገኙበት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ 9፡15 ሰዓት ይከፈታል። ቢሆንም 22ኛው ቀን የሥራቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋ/ኢ/ል/ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት።
- ለበለጠ መረጃ፦ 046-554-1393 / 0019/ ዱራሜ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የከምባታ
ጠምባሮ ዞን ፋይ/ኢኮ/ልማት
መምሪያ – ዱራሜ