የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ 005/2013
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ አስ/ር በኩል በዱራሜ ከተማ የሚገነባ የባህል ማዕከል ቀሪ ሥራዎች ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡- ስለሆነም
- ደረጃቸው GC-3/BC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- የዘመኑን ፈቃድ ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቶች 400,000/አራት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ዋስትና በሲፒኦ /የባንክ ጋራንት/ ማቅረብ የሚችሉ::
- ከዚህ በፊት በዞናችን ውስጥ ከዞን ማዕከልም ሆነ በወረዳዎች የግንባታ ጨረታ አሸንፈው እየሠሩ ያሉ ከሆነ የግንባታው ሥራ የደረሰበት ደረጃ 75% እና ከዚያበላይ ስለመድረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤ ያለበለዚያ ግን ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል እያንዳንዱ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማሸግና በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 8:30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ታሽጎ 8፡45 ይከፈታል፡፡ ቢሆንም 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ለበለጠ መረጃ፡- 046-554-1393 /1116/ ዱራሜ
የከምባታ ጠምባሮ ዞን
ፋይናንስ መምሪያ