የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ግልጽ
ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በ02 ቀበሌ እና በ04 ቀበሌ ለሚሰራው 3 ብሎክ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ለማሰራት በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች/ ተቋራጮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-
1. ደረጃቸው GC/BC 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
- ለሥራው ሕጋዊ አግባብነት ያለው ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና እድሳት ያደረጉ፤ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው ፣
- የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ ልማት ቤቶችኮንስትራከሽን ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 21/ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻው ዋና እና ኮፒ በማድረግ ስታሸገ ኤንቨሎፖች በኣብከመ የከሚሴ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራከሽን ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ ሁለተኛው ቀን /22 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ድምር 2% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር፡– 033 554 0255/0198 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
- ማሳሰቢያ ተጫራቶች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ተያይዞ መቅረብ አለበት ይህንን የማያሟሉ ከሆነ ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ውድቅ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በአብክመ የከሚሴ ከተማ ልማት
ቤቶች ኮንስትራክሽን ከተማ
አገልግሎት ጽ/ቤት