የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች
- ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ፣
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ ፣
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃ ፣
- ሎት 4 የግብርናና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና መገልገያዎች እና
- ሎት 5 ፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶች ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1(ደረሰኝ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ወይም በተናጠል ሊሆን ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ 100 /አንድ መቶ / ብር በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚታሸግ ድረስ ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334510464 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራቱን የጠበቀና ኦርጅናል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መግባት አለባቸው
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ከአቅራቢው ጋር የውል ስምምነት በሚፈፅምበት ወቅት የእቃውን መጠን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት
በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ/ኢ/ት/ጽ/ቤት