የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የኧሌ ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች፡
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች /የጽህፈት መሣሪያ ፣
- ኤሌክትሮኒክስ
- የስፖርት ትጥቅ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ጨረታ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ድርጅቶች /ተጫራቾች/፡-
- በዘርፉ የ2013 ዓ/ም የተደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁና ማቅረብ የምትችሉ፣
- በዘርፉ የ2013 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላችሁና ማቅረብ የምትችሉ፣
- በዘርፉ የግብር ከፋይነት የምስክር በረቀት ያላችሁና ማቅረብ የሚትችሉ፣
- በዘርፉ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላችሁና ማቅረብ የሚትችሉ፡
- በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላችሁና ማቅረብ የሚትችሉ፣
- በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላችሁና ማቅረብ የምትችሉ፣
- የዋጋ ማቅረቢያ በሚታይ ጽሑፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች CPO/የጨረታ ማስከበሪያ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ የተረጋገጠ 10,000.00/አስር ሺህ ብር ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የዕቃውን ዓይነት የያዘ ሠነድ (Specification) የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ግዥ 150/አንድ መቶ ሃምሳ/ ብር በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኧሌ ልዩ/ወ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ 150/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመከፈል ኧሌ ልዩ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ ሰነዱን መወሰድ ይችላል:: በአራቱ ዘርፎች የወጣጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ዕጩ ተጫራቾች
የጨረታ ሠነድ፡-
የጽሕፈት መሣርያ/አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/ለብቻ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ለብቻ የስፖርት ትጥቅ ለብቻ በአንድ አንዳንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክንካል እና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ እርጅናል እና አንደ አንድ ኮፒ ማለትም ቴክንካል ኮፒ -1 ፋይናንሻል ኮፒ -1ቴክኒካል ኦርጅናል-1 ፋይናንሻል ኦርጅናል በማድረግ በጨረታ ማስከበርያ /CPO/ ለያንዳንዱ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ጋር በትክክል በታሸገ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ማህተም በማሳረፍ አድራሻ በመግለጽ በመፈርም 16ኛው የሥራ ቀን 5፡30 ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 10/ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- 11/ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሰነድ 10% /አስር ፐርሰንት/ በማስያዝ ባሸነፉበት በ7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10,000.00/ አስር ሺህ/ ብር ለመንግሥት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- 12. ጨረታው ይከፈታል በተባለበት በ16ኛው ቀን በመንግሥት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 13/ ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ–ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም፡፡
- 14/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በአራቱ ዘርፎች መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶች በእያንዳንዱ መሞላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– 0920436294፣916702707
የኧሌ ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ኮላንጎ