< Back
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ የጽዳት እና ስቴሽነር ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር /ኦፖኮ ግጨ/16/2012
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ የጽዳት እና ስቴሽነር ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ከበጀትና ፋይናንስ ንዑስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር G-2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ በ15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ አጠናቆ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን ስራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎችም የማውረጃ እና የመጫኛ ወጪዎችን ሸፍነው ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መጋዘን አ/አበባ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ በ8/8/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8/8/2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ወረዳ 05 ላንቻ አካባቢ የቀድሞ አልፋ ዩኒቨርሲቲ ቤት ቁጥር :-372
ስልክ ቁጥር፡– 0118787093
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን