የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር /
ኦፖኮ ግጨ/20/2012
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሬዲዮ የመገናኛ እና ዝናብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል::
- ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት ቀናት ከበጀትና ፋይናንስ ንዑስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር G-12 በመቅረብ የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ::
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ በ30 (ሰላሳ) ቀን ውስጥ አጠናቆ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎችም የማውረጃ እና የመጫኛ ወጪዎችን ሸፍነው ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መጋዘን አ/አበባ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 15/10/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15/10/2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ 4፡ 30 ሰዓት ይከፈታል::
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ወረዳ 05
ላንቻ አካባቢ የቀድሞ አልፋ ዩኒቨርሲቲ ቤት ቁጥር 372
ስልክ ቁጥር: 0118787093
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት መስተዳድር
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን