የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ OACF, AMF/SNCB/02/2012
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች የተጋቡ የቀለም ቆርቆሮ፣ ዳሜጅ የሆነ የአውቶ መካኒካል፣ ኤሌክትሪካል ቤሪንግ፣ የባትሪ እቃዎች፣ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው ጋዜጣ እና አሮጌ Grainfrigers ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የ2011/2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን/የ2011 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አሰላ ቁሉምሳ በሚገኘው የፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 053 ወይም አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ቡናና ሻይ ልማት ሕንጻ ሥር ከሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ዘወትር በስራ ሰዓት፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ጠዋት ከ2:00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7:00-10:00 ቅዳሜ፣ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12/2013 ዓ.ም እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ብቻ አሰላ ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 017 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በዕለቱ መስከረም 12/2013 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ /ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 017 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ ስልክ ቁጥር፡– 022 331 14 44 ወይም 0223318197 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
ኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን
ኃ/የተ/አሰላ ብቅል ፋብሪካ