የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/BA01/2013
ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ጅባት ጌዶ ፤ በረክ ፤ እንጦጦ የካ ፧ ሱባ ሰበታ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የጊንድላ ፤ የአጣና ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ቀበና ሼል አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- የቁም ባህርዛፍ ደን ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 6% በማስላት ስባንክበተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 መደወል ይችላሉ
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት