የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2013
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና የ2012 ዓም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ብር 50/ሃምሳ/ ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ሙግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺ/በኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ ስም /cpo/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ወይም ዝግ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ከመስሪያ ቤቱ ጋር በሁለተኛው ቀን ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ቶነሮች/ኮምፒተር ቀለሞች፤ የኮምፒዩተር ወረቀት፣ ካርቦን፣ እስክሪፕቶ፣ፎቶኮፒ ቀለም፣ፍላሽ ዲስክ፣ዲቫይደር፣ከለርድ ወረቀት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0226611056 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት
ባሌ ቅርንጫፍ