የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/BA07/2012
ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣ
በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ፤ በረከ ፤ እንጦጦ የካ ፣ ጅባት ጌዶ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- የጊንድላ ፤ የአጣና ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያjኣጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታዉ የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- የቁም ባህርዛፍ ደን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 6% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0111240249 መደወል ይችላሉ
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት