የኦሮሚያ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም (ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተር እና ላፕ-ቶፕ) ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Tender
< Back

የኦሮሚያ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም (ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተር እና ላፕ-ቶፕ) ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን ለመ/ቤቱ 2012 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል፤

 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም (ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ) ከህጋዊ ቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት በማስታወቂያው ላይ መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ድርጅቶች ዝርዝር ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፣

 • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ እና አግባብ ያለው የታደሰ የዘመኑን 2012 . የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 •  ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዶክመንታቸውን ኮፒውንና ኦርጅናል በተለያየ ፖስታዎች 2 በሁለት ፖስታዎች እንዲሁም በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የሰነዶቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሠነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶከመንቶችን ኦርጅናልና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የዕቃ ናሙናዎችን እንዲያቀርቡ በመስሪያ ቤቱ ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸው፤
 • የዕቃው የርክክቡ ቦታ በኦሮሚያ የኦሮሚያ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን፤ተጫራቾች ጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ።
 • የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ለመወዳደር ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118360677 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

አድራሻ:- ሳር ቤት በሚገኘው የኦሮሚያ ህንጻ 7 ፎቅ መሆኑን እንገልጻልን።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ አካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለሙጥ ባለሥልጣን