የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2012 የበጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ ወንበሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ አስፈላጊ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
ስለሆነም፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥ ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው፣
- ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የዕቃውን ዓይነት በግልዕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎች ናሙና (Sample) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዘ እለባቸው።
- የጨረታ እሸናፊው የትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን እስከ መ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ ያቀርባል።
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 (አስራ ምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሙሉ ዶክሜንቶችን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤታችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 9ኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን መክተት አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቢሮው ለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 011-515-46-15 የኦሮሚያ ከሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አዲስ አበባ ፍላሚንጎ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ጽ/ቤት ጊቢ ውስጥ ነው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ