ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣
- ቋሚ ዕቃዎች፤
- ICT ዕቃዎች፤
- የፅህፈት መሣሪያዎች፤
- የተለያዩ የመኪና ቅባቶች፤ እና
- ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውንየሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዥ ኤጄንሲ የተሰጠ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና ሌሎች ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00(ሃምሳ ብር) በመክፈል ጨረታውን በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቦሌ መስመር ፍላሚንጎ ፊት ለፊት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ጽህፈት ቤት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ቀርበው የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0115-536972 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ
አዲስ አበባ