የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2012
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ ጽ/ቤቶች የሆኑ በክልል፣ በዞንና በወረዳ የሚገኙ
- የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፤
- ሞተር ሳይክሎች፤
- ጄኔሬተሮችና
- ቁርጭራጭ ብረታብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።
- የኤጀንሲው አድራሻ፣ አዲስ አበባ ሳርቤት ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ሳይደርስ ቤተልሔም ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 ሰዓት– 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከ3፡00 ሰዓት-11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓም ከጥዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0917813660 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ /ፊንፊኔ/ አዲስ አበባ CPOለማስራት፡-
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ/
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency