Air conditioning and Refrigeration / Computer and Accessories / Equipment / Laboratory Equipment and Chemicals / Networking Equipment and Installation / Telecommunication Equipment

የኦሮሚያ ሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዎል ማውንትድ ኤሲ ፣ ታብሌት እንዲሁም የተለያዩ የኔትወርክ ፤ የላብራቶሪ ፤ የጨረራ መለያና መለኪያ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

ዎል ማውንትድ ኤሲ፣ ታብሌት እንዲሁም የተለያዩ የኔትወርክ፤ የላቦራቶሪ፤ የጨረራ መለያና መለኪያ ዕቃዎች ግዢ

 የተጫራቾች መመሪያ

 1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
 4. የተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ መሆን የሚፈልጉትን ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መፃፍ ይኖርባቸዋል።
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስምና /brand name/ የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርበታል፡፡
 6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻያ ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡
 7. ቢሮአችን የሚያጫርተውን ዕቃዎች ብዛት ንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
 8. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጽም ኃላፊነቱ የአቅራቢ ድርጅት ነው፡፡
 9. የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ዓይነት (ናሙና) ዘወትር በሥራ ሰዓት /ቤታችን ድረስ ማምጣት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ናሙናውን ከወጣው ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ጋር ማስተያየት ያስፈልጋል፡፡
 10. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ሰፊደል የተጻፈው ይወሰዳል፡፡
 11. ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት /ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ያደርጋል፡፡
 12. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች ጭነው ለማቅረብ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ፡፡ ውሉ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 13. በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 14. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ በዋስትና ሰነድ የተያዘው ሲፒኦ ውል መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ተይዞ ይቆያል፡፡
 15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ማስከበሪያ ዋስትና የያዘውን ገንዘብ ለቢሮው ገቢ ይሆናል፡፡
 16. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
 17. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ላይ የዕቃዎቹን መስፈርቶች አይነት፤ መጠንና ብዛት በትክክል ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 18. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡
 19. ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ። ሆኖም ለአንድ ዓይነት ዕቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
 20. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (price validity day) ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ የሚፀናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቀው የሚያስረክብበት ጊዜ (delivery time) መግለጽ አለበት፡፡
 21. የዕቃችን ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆነ በኋላ ነው፡፡
 22. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍጹም አይቻልም፡፡
 23. ማኛውም ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1.5% የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 24.  ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በ16ኛው ቀን 500 ሰዓት ይዘጋል። በዚህ ዕለትም 530 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
 25. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሳቢያ፡ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አድራሻ፡ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኦሮሚያ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ብሎክ 2 ግራውንድ የሚገኝ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የኦሮሚያ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን