የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2013
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2013 በጀት ዓመት ሶቶሌ (የጆንያ መስፊያ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡
- የዘመኑን ግብር የገበሩ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴትታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዛችኋል። የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011-466-25-27/68 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ