የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መንግስት ህንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ለኦሮሚያ መስሪያ ቤቶች የጽዳት አገልግሎት እና የአትክልት እንክብካቤና ማስዋብ ሥራ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሣ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ፣ ሳር ቤት አካባቢ የኦሮሚያ መንግስት ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ወቅታዊ የግብር ክፍያ ግዴታቸውን የተወጡ እና በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃዎች አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጽዳት አገልግሎት እና የአትክልት እንክብካቤና ማስዋብ ሥራ አገልግሎት ብር 4000/አራት ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም CPO የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በተከታታይ ለ15/አስራ አምስት/ የስራ ቀን ውስጥ በድርጅቱ የግዥና፤ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አሽገው ፣ በ16ኛው ቀን እስከ 4፤30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ እለት ወዲያውኑ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- .ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቀጥር 011 3690193 /0911185103 /0919320664 መደወል ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ በመንግስት ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት