Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle / Water Engineering Machinery and Equipment

የኦሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ድርጅት በ2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የመንገዶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ፣ ገልባጭ መኪኖችን ፤ አነስተኛ የመስክ መኪኖች፤ የውሃ ቦቴ መኪኖችን፤ እና ሚክሰር ትራክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ 

ግልጽ ጨረታ ቁጥር ኦ.መ.ኮ.ድ.22/2012 

የኦሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኦመኮድ) በ2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የመንገዶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣ ገልባጭ መኪኖችን፤ አነስተኛ የመስክ መኪኖች፤ የውሃ ቦቴ መኪኖችን፤ እና ሚክሰር ትራክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ የሚፈለገው መሳሪያ ዓይነት እና የሚከራይለት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ዝርዝር ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ መመሪያ ሠነድ ወስጥ ተመልክቷል፡፡ 

በመሆኑም በጨረታው ስመሣተፍ የሚፈልጉ :

  1. ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው እና በ2012 በጀት ዓመት ታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግሥት የግብር ግዴታን ስለመወጣቱ የሚያመለክት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ከሚመለከታቸው ገቢዎች ባለሥልጣን፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያመላክት እና ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ /TIN/ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በተራ ቁጥር 1 ሥር የተጠቀሱትን ሠነዶች ፎቶ ኮፒ ከማመልከቻ ጋር አያይዞ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከድርጅታችን ቢሮ ቁጥር 14 (2ኛ ፎቅ) በሚከተለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የማይመለስ የክፍያ መጠን በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ 

.  

የሚፈለገው የአገልግሎት አይነት 

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (ብር

1

ለኮንስትራክሽን መሣሪያዎች 

300.00

2

ለገልባጭ መኪኖች 

200.00

3

ለውሃ ቦቴ መኪኖች 

200.00

4

ለአነስተኛ የመስክ መኪኖች 

200.00

5

ለሚክሰር ትራክ 

150.00

3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ “CPO” ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional & lrrevocable Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው። 

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት አይነት ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

5. ጨረታው በዚሁ ዕለት ማለትም ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በሚገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቁጥር 3 (2ኛ ፎቅ) ይከፈታል፡፡ 

6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡- ቃሊቲ የመካኒኮችና አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ 

ስልክ ቁጥር፡- 011-439-16-80 /011-439-17-82/011-439-11-94 

ፋክስ: 011-439-02-42 

የኦሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ድርጅት