ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በተቋሙ ህንጻ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሊፍት/አሳንሱር ድራይቭር በመበላሸቱ
- II ኪሎ ዋት የሊፍት ድራይቭ (IIkw/15HP) Lift Dirive)
- የወርሀዊ ፍተሻ እና ዓመታዊ የሰርቪስ አገልግሎትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ብር በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀ ሰነድ መግዛት የሚችል ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን ከተቋም ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ በሁለት በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርጎ ዋናና ኮፒ ብለው በአንድ እናት ኤንቬሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ን/ጠ/አገ/ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 15ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በካሽ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊ የሆነ ድርጅት በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታእስከ ዋና መ/ቤትድረስማቅረብናማስረከብ ይኖርበታል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢያዎች/ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቀጥር 0462125214 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
- ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የተቋሙ አድራሻ፡- ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
- አድራሻ፡- ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሞቢል በሚወስደው መንገድ ከጠቅላይ ፍ/ቤት አለፍ ብሎ
የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
ሀዋሳ