ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብአቶችን በተዘረዘሩት መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የበጀት ኮድ 6211 ሎት 1 የደንብ ልብስ፡፡
- የበጅት ኮድ6212 ሎት 2 አላቂ የጽህፈት መሣሪያ፡፡
- የበጅት ኮድ 6215 ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፡፡
- የበጀት ኮድ 6218 ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፡፡
- የበጀት ኮድ 6219 ሎት 5 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፡፡
- የበጀት ኮድ 6313 ሎት 6 የማሽነሪ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡፡
- የበጀት ኮድ 6314 ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች፡፡
- የበጀት ኮድ 6213 ሎት 8 የተለያዩ ህትመቶች፡፡
በተጨማሪ ት/ቤቱ የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ጥገና፣ የማሽነሪ ጥገና ፤የኤሌትሪክ መስመር ጥገና የኮምፒውተር ሶፍትዌር ዝርጋታ፤ አወዳድሮ ለማስጠገን እና የድንብ ልብስ ስፌት አወዳድሮ ለማስፋት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ሲወዳደሩ ሲመጡ ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች:
- የዘመኑን ግብር ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመረጠ ሰርተፊኬት ያለው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬት ያለው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማሰያዝ ይኖርበታል ::
- በጨረታው ላይ የቀረቡትን እያንዳንዱ ዕቃዎች ማለትም በሎት 1፣ በሎት 2፣ ሎት 3፣ ሎት 4 እና በሎት 5 በሙሉ የተገለጹትን ዕቃዎች ማለትም ሳምፕል (ናሙና ) ማቅረብ የሚችል እና ሎት 6፣ ሎት 7 በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ያለበት ሲሆን ነገር ግን በከፈል ናሙና ያቀረበ ተጫራች ናሙናውን ያቀረበባቸው ዕቃዎች ላይ ብቻ ነው መወዳደር የሚችለው፡፡
- ከላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሁለት በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር ) በማስያዝ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃዎች ዋጋ ላይ ቫት ማስገባት አለበት::
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0112-13-51-89
አድራሻ ፡– አብነት ቁጥር 2 ክኒሊክ ወደ ውስጥ የሚያስገባ አስፓልት አለሙ ሜዳ 100 ሜትር ከፍ ብለው ያገኙናል፡፡
የኦሜድላ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት