የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር እዩ 03/2013
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2013 በጀት ዓመት ለተለያየ የህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 01 የአርማታ ብረት
- ሎት 02 የላብራቶሪ ዕቃዎች
- ሎት 03 የማገዶ እንጨት
- ሎት 04 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
1. አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነው።
2. በጨረታው መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸው ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሎት 100.00/ አንድ መቶ ብር /ብቻ በዩኒቨርሲቲው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 006 በመግዛት ዕቃው የሚሸጥበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 006 ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር / ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
5. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ። የሚገዛዉ ዕቃ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል ።
6. የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ /ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ።
7. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃዎች የትራንስፖርት ማጓጓዣ ፣ የጫኝና አውራጅ ወጭዎችን እንዲሁም ከዕቃ ማጓጓዥ ጋር ያሉ ወጭዎችን ዩኒቨርሲቲው ግቢ ድረስ በራሳቸው ወጭ በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው ።
8. የጨረታ ሰነዱ መሸጥ የሚጀምረው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡30 ይከፈታል። ለሁሉም ጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል ። በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓት ተገዥ ይሆናሉ ።
9. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 /ሰባት/ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀን ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው ።
10. ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የድጋፍ ደብዳቤ አስፅፈው የሚመጡ አቅራቢ ድርጅቶች የድጋፍ ደብዳቤ ከሚፃፍላቸው መ/ቤቶች የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነት እና የሎቱን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ተገልጾ ጨረታውን ላወጣው መ/ቤት በአድራሻ መጻፍ አለበት ። ከዚህ ውጭ የሚመጡ ተጫራቶች ተቀባይነት የላቸውም ።
11. ዩኒቨርሲቲው ግዥ ለመፈፀም በአወጣው የአርማታ ብረት ጨረታ ላይ በተቀመጠው የቴክኒካል መገምገሚያ መስፈርት መሰረት የሚጫረተው አቅራቢ ድርጅት ግልጽ እና በሚታይ መልኩ ዶክመንቶችን አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት ።
2. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
13. ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ጨረታ ላይ 20% የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0588270621 ወይም በአካል ዩኒቨርሲቲው ድረስ በመምጣት መጠየቅ ይቻላል ። ለተጨማሪ ማብራሪያ የዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት www.inu.edu.et መጎብኘት ይችላሉ ።
15. በሎት 01 የአርማታ ግዥ ላይ የማጓጓዣ እና ሌሎች ወጭዎችን ዩኒቨርሲቲው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ