የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 008/2012
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኝው አስተዳደር ጽ/ቤት የG +3 ቢሮ ግንባታ በእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፦
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TUN/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው በመሆኑም ተቋራጮች በህንጻ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ አራት (BC-4) እና ከዚያ በላይ የሆኑ እንዲሁም በጠቅላላ ስራተቋራጭነት ደረጃ አምስት (GC-5) እና ከዚያ በላይ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውልይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ምድብ እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድና መመሪያ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ደረስ ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም ዓይነት ግብር የሽፈነ መሆን አለበት በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መስሪያ ቤቱ፡ ተጠያቂ አይሆንም።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛመሆን አለበት::
- መስሪያ ቤቱ፡ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወይም ጥሬ ገንዘቡን በመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ደረሰ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ቴክኒካል ዋናና ኮፒ ፋይናንሻል ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች በእ/ወ/ግ/ን/አስ/በድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ ቀናት እስከ 21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ( ተመስረቶ) መጫረት አይቻልም::
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ጨረታው በ21ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል: ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ እንዲከፈት በማድረግ ወድድሩ ይካሄዳል ::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ብሔራዊ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ::
አድራሻ: ከአዲስ አበባ ለሚ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል::
ከደብረ ብርሃን 83 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 011 119 02 70/280 ደውለው መረጃ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡:
የእ/ወ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ ቤት/የግ/ን/አስ/ቡድን
ለሚ