ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የእብናት ወረዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የኤሌክትሪክሲቲ ኤሌክትሮኒክስ ፣
- ሎት2 የICT Departemnt ፣
- ሎት3 ኮንስትራክሽን ፣
- ሎት4 የብረታ ብረት ፣
- ሎት5 የአኒማል ፕሮዳክሽን ፣
- ሎት6 የክሮፕ ፕሮዳክሽን ፣
- ሎት7 የፈርኒቸር ፣
- ሎት8 የአውቶሞቲቭ ፣
- ሎት9 የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
- ሎት 10 ህትመት
- ሎት11 የጋርመንት ዲፓርትመንት በግልጽ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ የመወዳደሪያ መስፈርቱ እንደሚቀጥለው ተቀምጧል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
- ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 70 ብር በመክፈል በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ መለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ኮሌጁ የሚገዛውን ዕቃዎች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው አንድም ዕቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- የሚገዙትን ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ መታወቂያ በበኩር ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ኮሌጁ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል፡፡
- ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው /ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ /የህዝብ /ብዓላት ከሆነ በቀጣዩ በስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ስዓት ታሽጎ በ5፡ 00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን ዕቃዎች ለእብናት ወረዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊውን የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0584400571/395 /0584400858 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት ወረዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ