Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Vehicle

የኣማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተለያዩ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

የማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ

የኣማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ 2013 በጀት ዓመት ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ የውሃ ቦቴ፣ ዋገን ድሪል፣ ሎቤድ እና ሰርቪስ መኪና በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ  የተለያዩ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
 3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤(ሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ።)
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
 5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡
 6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለውሃ ቦቴ፣ ለሎቬድ፣ ለገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለገልባጭ መኪና .ኩብ እና ለሰርቪስ መኪና ለአንድ ተሽከርካሪ የሚያስይዙት ብር 10,000.00 (አስር ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ ፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60(ስልሳ ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እወቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ቢሮ ቁጥር 02 ይህ ማስታወቂያ ኣየር ላይ ከዋለበት ቀን 12/02/2013 . ጀምሮ እስከ 27/02/2013 . መግዛት ይችላሉ፡፡
 9.  ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ከግዥ አፉሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 27/02/2013 . 8.00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራከሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ 27/02/2013 . ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 830 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
 11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 12. የጨረታ ሰነዱን ለኤጀንሲው ድረገጽ WWWarrca.gov.et በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፡፡
 13. በጨረታው ለመሳተፍ ያሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ

ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-1100

በስልክ ቁጥር 058-220-51-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህር ዳር