ፌ/ፐ/ኮ፡– 07/2012
የኢፌዴሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 በጀት ዓመት የዋናው ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ (Control Room, Watch Tower Fence and Electronic System Works) ለማሰራት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ወቅታዊ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ፌ/ፖ/ኮ 07/2012 የዋና ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ ለማሰራት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (BID BOND) /CPO/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፌ/ፖ/ኮ 07/2012 የዋና ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ ለማሰራት እስከ 19/12/2012 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዲቪዥን ቢሮ ቁጥር 203 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሸግና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ወይም በመልዕክት ሣጥን ቁጥር 199 መላክ ይችላሉ፡፡ መቤታችን ስለጨረታ ሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም::
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከላይ በተገለፀው የጨረታ ሰነዱ የመከፈቻ የመጨረሻ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው በተመሳሳይ ቀን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ትንሹ አዳራሽ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5-58-17-39/011-5-52-4412/011-5-31-20-95/07-5-31-21-99 የውስጥ ስልክ 2104/1107/1101 ፋክስ ቁጥር 011-5-52-5517 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን