የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ፌ/ፖ/ኮ-11/12/2013
የኢፌዲሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል ፡
- 1ኛ.የተለያዩ የመመገቢያ ዕቃዎች
- 2ኛ የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ወቅታዊ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ፌ/ፖ/ኮ/11/2013 የተለያዩ የመመገቢያ ዕቃዎች ግዥ 6,000.00 (ስድስት ሺህ ብር) እና ፌ/ፖ/ኮ/12/2013 የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ 9,000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (BlD BOND) /CPO/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፌ/ፖ/ኮ 11/2013 የተለያዩ የመመገቢያ ዕቃዎች ግዥ እስከ 04/03/2013 ዓም ፌ/ፖ/ኮ 12/2013 የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ እስከ 8/03/2013 ዓም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዲቪዥን ቢሮ ቁጥር 203 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማሸግና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ወይም በመልዕክት ሣጥን ቁጥር 199 መላክ ይችላሉ::
መ/ቤታችን ስለጨረታ ሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም።ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከላይ በተገለፀው የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው በተመሳሳይ ቀን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ትንሹ አዳራሽ በ4፡30 ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5-58-17-39/011-5-52-44-12/011-531-20-95/011-531-2199 የውስጥ ስልክ 2104/1107/1101 ፋክስ ቁጥር 011-552-55-17 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን