የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢመደኤ ግልፅ ጨረታ መደበኛ 01/2013
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተለያዩ የእቃ ግዢዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሀ. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ–ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ወይም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ለ. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት፣ ቲን እና ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለስልጣን የሚሰጥ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሐ. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- መ. በአማርኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ማግስት ጀምሮ ከኤጀንሲው ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ሠ. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታ ሰነዱን በነፃ ማግኘት የሚችሉት ካቋቋማቸው አካል ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ሲሆን ደብዳቤ ሲያፅፉ የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ማስጠቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ረ. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ CPO ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ኣገልግሎት ዋስትና መሆን አለበት፡፡
- ሰ. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን እና ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ቀጥሎ በሰንጠረዥ ተገልጿል፡፡
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት |
ሎት 1:- የጽህፈት እቃዎች |
6,035.66 |
በ13-02-2013 ዓም በ8፡30 ሰዓት ይዘጋል፡፡ |
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ3/2/2013 ዓም በ8፡35 ሰዓት ይከፈታል
|
ሎት 2፡– የጽዳት እቃዎች |
9,761.45 |
||
ሎት 3-የመኪና መለዋወጫ እቃዎች |
6,275.36
|
||
ሎት 4- አልባሳት
|
9,297.24
|
||
ሎት 5፡– የህንጻ መሳሪያ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች |
5,892.09
|
ሸ.ተጫራቾች ለሎት 4 እና ሎት 5 የግዥ ዓይነቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንዲሁም ለሎት 1, 2, 3 የፋይናንሻል ሰነድ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
ቀ ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስድራሻ፡– ቦሌ ወሎ ሰፈር ከአይቤክስ ሆቴል አጠገብ አዲሱ
የINSA ህንፃ ላይ ሰልክ ቁጥር +251990408609
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ