ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግ/ጨ/ቁ/03/2012 ዓ/ም
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የኢት ፖሊስ/ዩኒቨ/ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ለመ/ ቤቱ አገልግሎት የሚውል (CBC Machine (Human Count 30 TS) CENETRIFUGE (HU Max 4k) በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ድርጅቶችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ተወዳዳሪ ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸውና ማወቅ ያለባቸው ነገሮች፡
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ Vat/ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
- በመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ በዕቃ አቅራቢነት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የዘመኑን የግብር የከፈሉና ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ የህክምና መሣሪያ ማሽኖች ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ፣የባንከ ጋረንቲ / Bid Bond/ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ልደታ ክ/ከተማ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቢሮ የማይመለስ ብር 100.00 አንድ መቶ ብር ከፍለው ሙግዛት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዶቻቸው ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ተብሎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነት ደብዳቤ ሲደርሳቸው ኢትIፖሊ/ዩኒ/ኮሌጅ ሰንዳፋ ድረስ በመምጣት ውል ሙግባት አለባቸው
- ተጫራቶች ያሸነፉባቸው ዕቃዎች ኢትፖሊየዩኒ/ኮሌጅ ግ/ቤት ሰንዳፋ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ5ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋል:: በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች በእቃው ጥራት ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን ስተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ባለው ዝርዝር ዕቃዎች መሰረት የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ሞልተው ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለምትወዳደሩባቸው እቃዎች በድርጅታችሁ ውስጥ ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሙያተኞች ናሙና ወይም እቃውን የሚገልጽ የናሙናውን ካታሎግ ማሳያት ይኖርባችኋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 01- 686 05 70 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ
ኮሌጅ ሠንዳፋ