የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የቤተ መንግስት አስተዳደር ጨረታ ቁጥር PA/NCB/007/2013
- የፕሮቶኮል ልብስ፣ የስራ ልብስ፣ የፕሮቶኮልና የስራ ጫማ
- ጨረታ ቁጥር PA/NCB/008/2013
- ምድብ አንድ፡– የጽህፈት መሳሪዎች እና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ምድብ ሁለት፡– የጽዳት አላቂ ዕቃዎች
- ምድብ ሶስት፡– ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው ቤተመንግስት አስተዳደር በመገኘት ከላይ በምድብ ተከፋፍለው ለተጠቀሰት ዕቃዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለጨረታቁጥር የA/NCB/007/2013 የጨረታ ዋጋውን 2% ለጨረታ ቁጥር የA/NCB/008/2013 ለምድብ አንድ የጨረታ ዋጋውን 2% ፤ ለምድብ ሁለት የጨረታ ዋጋውን 2%፣ እና ለምድብ ሶስት የጨረታዋጋው 2% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን በስራ ሰዓትና እና 16ተኛ የስራቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማያያዝ ቤተመንግስት ቅጥር ግቢ 5ተኛ በር ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ60 (ስልሳ ቀን) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘብት በለቱ ከቀኑ በ8፡30 ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ስዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አደራጃ፡ ፍልውሃ አካባቢ ቤተመንግስት አስተዳደር 5ተኛ በር
ስልክ ቁጥር፡– +2515150296/0115548794
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
መንግሥት የቤተመንግስት አስተዳደር