የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክስዮን ማህበር
የህንፃ ግዢ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0002/20
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህንፃዎች ያሏችሁና ለመሸጥ ፍላጐት ያላችሁ ባለንብረቶች ወይም ተወዳዳሪዎች በዚህ ግልፅ ጨረታ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
ሀ/ ህንፃው የሚገኝበት አካባቢ (Location)
- ሜክሲኮ አካባቢ፣
- ቸርችል ጐዳና፣ ሰንጋተራ፣ ብሔራዊ ቲያትርና ለገሃር፣
- ከመስቀል አደባባይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ፣
- ከቤተ መንግሥት ካዛንችስ በኡራኤል – ቦሌ መድሃኒያለም ብራስ ሆስፒታል፣
- ከባምቢስ ኦሎምፒያ እስከ መስቀል ፍላወር፣
- ከጐተራ በወሎ ሰፈር መንገድ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡
ለ/ ህንፃው ያረፈበት ቦታ (Area)
- ህንፃው ያረፈበት የቦታው ስፋት፡ ቢያንስ ከ400-500 ካሬ ሜትር ወይም ከዚያ በላይ የሆነ፣
- አጠቃላይ የቦታው ስፋት፡ ከ600-800 ካሬ ሜትር ወይም ከዛ በላይ የሆነ፣
- ህንፃው ቢያንስ ስድስት ወለል ያለው፣
- በቂ የመኪና ማቆሚያ (Parking Area) በምድር ቤትና በግልፅ ማቆሚያ ስፍራ ያለው፡፡
ሐ/ ህጋዊ መስፈርቶች
- የህንፃውን ህጋዊ ባለቤትና ይዞታ፣ ሙሉ ስምና አድራሻ እንዲሁም ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ህንፃው የሚሸጥበትን ዋጋ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቦታው ህጋዊ ይዞታነት በከተማው ማስተር ፕላን የተደገፈ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ፣
- የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከ2 እስከ 10 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድንና ቅፅ ከዋናው መሥሪያ ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ሰኔ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በውድድሩ ወቅት ባለንብረቶች ሁሉንም ህጋዊ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ.
አፍሪካ ጉዳና ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ
6ኛ ፎቅ በመቅረብ ወይም
በስልክ ቁጥር፡– 0115575757/0913 035168/0965 567832 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ