የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡– 002/2013
የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በታች ለተገለጹት ዕቃዎች ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የጽ/መሣሪያዎች
- ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 3. የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- ሎት 4. ፈርኒቸር
- ሎት 5. የአይቲ ዕቃዎች
- ሎት 6. የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች
- ሎት 7. የተለያዩ ህትመቶች
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በመስኩ አግባብ ያለው የታደለ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ የተመዘገቡበትን ማያያዝ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ፡፡
- ከተቁ 1 -7 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ለሎት 1-3,000፣ ለሎት2–3,000፣ ለሎት3-4,000፣ ለሎት4-3,000፣ ለሎት5-3,000፣ ለሎት 6 – ብር 4000፣ ሎት7- የተለያዩ ህትመቶች 4000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዩቤክ ኮሜርሻል ሴንተር (ሰንጋ ተራ) በሚገኘው 9ኛ ፎቅ የግዥ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በሎት 1- 5 ለተገለጹት ግዥዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች ኤጀንሲ እኤ.ኣ 2012 ባወጣው ደረጃዎች መሰረት የማረጋገጫ ዝርዝር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ በቀረበው ዝርዝር ውስጥ እስታንደርድ ላወጣላቸው ዕቃዎች ናሙና መቅረብ አለበት ለተባሉ ዕቃዎች በሙሉ ናሙናዎቹ ካልቀረቡ እና በተገለጸው እስታንደርድ መሰረት ካልሆነ ዋጋው ተቀባይነት አይኖረውም:: ናሙናዎቹ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሁሉም ሎቶች ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነዳቸውንና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነት (ሎት) በፖስታው ላይ በመጻፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሆኖ እስታንደርድ ላላቸው በቀረበው ዝርዝር ( specification) መሰረት ይቀርባል፡፡ እስታንደርድ ለሌላቸው ለሁሉም ናሙና የሚቀርብባቸው ስለሆነ መ/ቤታችን ባቀረበው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለጸው ዝርዝር (specification) መሰረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡–ዮቤክ ኮሜርሻል ሴንተር (ሰንጋ ተራ)
9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 905
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-5546807/011-5504837
የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት
ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን