የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት
- የተለያዩ የደንብ ልብስ እና
- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም
- የተለያዩ የጽህፈት መሳሪዎችን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በቅደም ተከተል መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተረዘረዘሩትን መስፈርቶ የሚሟሉ በዘርፉ የወጣ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(የቲን ) ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገፅ ላይ መዝገቡን የሚያሳይ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ስር በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተመሰከረለት በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት ስም አሠርተው ከጨረታ ሰነዳቸው (ከቴክኒክ ፕሮፖዛል) ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል”
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ባሉት ተከታታይ 16 /አስራ ስድስት/ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 11፡30 ሰዓት ከኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት ግን ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የዋጋና የቴክኒክ መግለጫዎች ለየብቻ በማየት ለእያንዳንዱ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን የጨረታውን ሥምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኢንስቲትዩቱ ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል በጨረታው መክፈቻ ዕለት አይከፈትም:: ነገር ግን ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ እለበት፡፡
- ጨረታው ከዚህ በታች በወጣለት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንስቲትዩቱ – ዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 313/314 በኢንስቲትዩቱ የስብሰባ አዳራሽ ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ |
የግዥ ዓይነት |
የጨረታው መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን /በብር/ |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
||
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
||||
1 |
|
ኢት.አ.ደ.አ./002/2012 |
ለሎት አንድ ብር አምስት ሺ (5,000)፣ለሎት ሁለት ብር አምስት ሺ/5,000/. |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 የሥራ ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
|
4፡00 ሰዓት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 የሥራ ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ |
4፡30 ሰዓት |
የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት