የጨረታ ማስታወቂያ
የሬዲዮ ቀጥታ ስርጭት ጨረታ
የኢትዮጵያ የኘሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የ16ቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሜዳቸዉና ከሜዳቸዉ ዉጭ የሚያደርጉትን ዉድድር በሬዲዮ የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ለይቶ ማቅረብ አለባቸዉ እነርሱም ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል የሚገልፅ ዝርዝር ያካተተ መሆን ይገባዋል::
ቴክኒካል ፕሮፖዛል ግዴታዎችን የያዘ ሲሆን ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ለእያንዳንዱ አመት መወዳደሪያ የገንዘብ መጠን ይይዛል::
ተጫራቾች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማሟላት አለባችው
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ዉስጥ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ::
- ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል የሚገልፅ ዝርዝር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽገዉ ወሎ ሰፈር በሚገኘዉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:: ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ማሳሰቢያ:- የኢትዮጵያ የኘሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተበበቀ ነዉ::