የሰራተኞች ሰርቪስ መኪና ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ሰላሳ ሰው የሚጭኑ ሶስት ሚድ ባስ ተሽከርካሪዎችን የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ በኢትዮጵያ ብር መግዛት ይፈልጋል :: በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች :
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትን የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግዥና አቅርቦት ቢሮ በመገኘት የንግድ ፈቃድና ሌሎች ህጋዊ ሰነዶችን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተሽከርካሪዎቹን የሚያቀርቡበት ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በሰም በማሸግና አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የቴክኒካል እና የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ፖስታ በማድረግና ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ በማጠቃለል ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይታሸግና በዕለቱ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል የሚከበርበት ቀን ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው ታሽጎ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታው ያሸነፉበት ዋጋ የመልካም ስራ አፈጻጸም 10% የአፈፃፀም ዋስትና ያቀርባሉ፡፡
- ድርጅቱ የግዢ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ቦሌ ከፍስ ከተማ ወረዳ 6( አምቼ አጠገብ)
የቀድሞ የኢትዮጵያ ጥራትና የደረጃዎች ባስሥልጣን ገቢ ውስጥ
ስልክ ቁጥር፡- 0116 67 02 51, 011 8 69 5039 ፋክስ 0116459720 T.ሳ. ቁጥር 11145 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት