ያገለገሉ ጎማዎች ሽያጭ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢባትሎአድቃቅ 05/2012
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታብረት እና ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቃለቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ቅ/ጽ/ቤት ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከሚዘጋበት ቀን 4፡00 ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት ቃሊቲ ቅርንጫፍ በማለት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለአንድ ወይም ከአንድ በላይ ለሆነ ምድቦች እና ለንዑሳን ምድቦች መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ከ1ኛ እና 2ኛ ከወጡ በስተቀር ተሸናፊ ለሆነት ደብዳቤ ከደረሳቸው እስከ 15 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማስታውቂያው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል: ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ለሽያጭ ከቀረቡትና ያገለገሉ ጎማዎች ሙሉ በሙሉ መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉት ያገለገሉ እቃዎች አጠናቅቀው ማንሳት አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-4-40 40 78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት