ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር መ/መ/ተ/ 001/2013
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ ፡-የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች
- ሎት ሁለት ፡-የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
በዚህም መሰረት፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የአቅራቢነት ፍቃድ እውቅና ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ /15/አስራ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠ/አገልግሎት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000(አስር ሺህ) ብር በንግድ ባንክ፣ህብረት ባንክና ኦሮሚያ ህ/ስ/ባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በ 2(ሁለት) ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት በኋላ ባሉት 15(አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርባቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- . ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በአስራ አምስተኛ (15) ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
- . በተጫራቾች የሚሞላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና በግልጽ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
- . ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራርያ፡- በስልክ ቁጥር 0221162194 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት