የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ብግጨ/ኢሕጤኢ/ግኬቲ/Aud.Vid/056/2013 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአንድ ዓመት ሳይቀየር በሚቆይ ዋጋ የAudio and video production ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፤ TIN NO ያላቸው፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ ተመላሽ የሚሆን ብር 10000.00/አስር ሺህ ብር ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዝርዝር መገለጫን የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ሰነዶችን ለያይተው በመግለፅ አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት እና በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እና እሁድ ሳይጨምር/በኢንስቲትዩቱ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን፤ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ክፍል በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈፃፀም/ውል ማስረከቢያ በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንስቲትዩቱ ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0112 771056/771054 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
/የቀድሞ ፓስተር ኢንስቲትዩት/
አዲስ አበባ