የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች በተመለከተው ኮርስ ላይ ሥልጠና ሊሰጡ የሚችሉ ተጋባዥ ኮንሰልታንቶች አሰልጣኝ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ቢሮ ተገኝታችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተ.ቁ |
የሥልጠና መስክ የድሪሊንድ መሣሪያዎች ጥገና ሥልጠና |
ተፈላጊ ችሎታ
|
ሎት 1
|
Training in Drilling Technology and Well rehabilitation and diagnosis course
|
–አመልካቹ ድርጅት ከሆነ በተጠቀሰው/በተጠቀሱት የሥልጠና ዘርፎች በማሰልጠን እና በተግባር ሥራ ላይ ቢያንስ የ4 ዓመት ልምድ -አመልካቹ ግለሰብ ባለሙያ ከሆነ በተጠቀሰው በተጠቀሱት የሥልጠና ዘርፎች በማሰልጠን እና በተግባር ሥራ ላይ ቢያንስ 6 ዓመት ልምድ ያለው
|
ሎት 2
|
GIS & Remote Sensing
|
|
ሎት 3
|
Geophysical Groundwater Investigation
|
|
ሎት 4
|
Groundwater modeling
|
ማሳሰቢያ፡
- ተወዳዳሪው ድርጅት ከሆነ፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ሰነድ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ (TIN) ሰነድ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የተዘጋጀውን (TOR) በምዝገባ ወቅት መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ሎቶች ለእያዳንዳቸው በተናጠል ለሥልጠናው የሚጠይቁትን ክፍያ መግለጫ ለብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 4 70 87 24 ወይም 0114709663 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቃሊቲ አደባባይ ከባቡር ተርሚናል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ. የግዥ፣ ፋይናንስ፣ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ 3ኛ ፎቅ መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት