የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፤
ባዶ የዘይት በርሜሎት፤ባዶ የአስፋልት
በርሜሎት እና ቁርጥራጭ ብረታ
ብረቶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ
አወዳድሮ ለመስኖ የጨረታ
ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢኮስኮ ዲማ–ራድ ድ/መ/ግ/ፕ ቲ-001/2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በዲማ–ራድድ/መ /ግ/ ፕሮጀክት የሚገኙ
- ባዶ የአስፋልት፤ የዘይት በርሜሎች፣
- የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች፤
- የተለያየ አምፒር ያላቸውን ያገለገሉ ባትሪዎች እና
- ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ህትመት እና ማባዣ ከፍል በኣካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፈ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርበው ሲሆን የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው::
- ተጫራቾች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ የሚያደርጉበት የ ጨረሻ ቀን ግንቦት 08 ቀን 2012 ዓ ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ከ10 በመቶ /10%/ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጠ ቼክ CPO ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 01 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ሜክሲኮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የስልክ ቁጥር፡– 0929095153 /0953841584 /0911908534 /0902339701
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች
ኮርፖሬሽን የዲማ–ራድ ድልድይ
መንገድ ግ/ፕርጀክት