የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ቦሌ ቡልቡሳ ጥ/ጉ/ው/
ሚ/ቧ/መ/ዝ/ፕሮጀክት ቲ-03/2012
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በውሃ መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የቦሌ ቡልቡላ ጥ/ጉ/ው/ማ/ቧ /መ/ዝ/ፕሮጀክት ለፕሮጀከት መንገድ ስራ አገልግሎት የሚውል ገረጋንቲ ከነማጓጓዣው SELECT MATERIAL WITH TRANSPORT በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ያልተመዘገበ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይችላሉ:
- የመጫረቻ ሰነዱ የሚዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው::
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቂሊንጦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት የኢትጵያ ንግድ ባንክ የሚገኝበት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከሚገኘው የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማናቸውም አቅራቢ ክፍት ነው የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ፣ ወይንም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ቂሊንጦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገኝበት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከሚገኘው የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ነሐሴ 7 ቀን 2012 ዓም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡15 ሰዓት ቂሊንጦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሸኝበት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከሚገኘው የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቶች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላል: : የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በውሃ መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የቦሌ ቡልቡላ ጥ/ጉ/ው/ማ/ ቧ/መ/ዝ/ፕሮጀክት
የስልክ ቁጥር 01 888 68 96
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች
ኮርፖሬሽን የውሃ መሰረተ ልማት
ኮንስትራክሽን ዘርፍ
የቦሌ ቡልቡሳ ጥ/ጉ/ው/ማ/ቧ/ መ/ዝ/ፕሮጀክት