ያገለገሉ ከባድና ቀላል
ተሽከርካሪዎች፣የኮንስትራክሽን
ማሽነሪዎች አና መሣሪያዎች መሸጥ
የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኮስኮቲ 86/2012
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ አይነት
- ያገለገሉ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች እና
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽነሪዎች ለመሸጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች/ግለሰቦችን በጨረታው ይጋብዛል፡፡
- ለ 2012 ዓ.ም የሥራ ዘመን የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተ.እ.ታ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋዮች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ወይም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ወይም የ2011 ዓ.ም የቀበሌ መታወቂያ ያሳደሱ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር / ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 5 ቀን 2012 ዒ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 20% (ሃያ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለ3 ወራት የሚቆይ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልተው ከፍተኛዋጋ የሚያቀርበው ሲሆን የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው።
- ጨረታው ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የኮርፖሬሽኑ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር 011 89 62 99
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች
ኮርፖሬሽን
የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን