የጨረታ ማስታወቂያ
ጨ/ቁጥር ኢኮስኮቲ-69/2012
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባለ Kuraz right bank main canal Structure Work መግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማግኘት ይችላሉ።
- የመጫረቻ ሰነዱ የሚዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው። የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ከጠቅላላ የመጫረቻ ዋጋ ከ1% ያላነሰ ወይም ከብር 500,000.00 ያልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይንም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ወጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ነው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ቀን ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጥቅል ግዥ ቡድን
ፓስታ ሳጥን ቁጥር 21952/1000
የስልክ ቁጥር 0118962991/0118723086
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን