የጨረታ ማስታወቂያ
ጨ/ቁጥር ECWCT/NCB/PG-41/2013
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች (Stationary) መግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን ግልጽ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዋናው መ/ቤት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ከጠቅላላ የመጫረቻ ዋጋ ከ1% ያላነሰ ወይም ከብር 500,000.00 ያልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ ወይንም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የግዥ መምሪያ ቢሮ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ታኅሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታኅሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራከሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በግዥ መምሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥር 0118962991/0118 72 30 86 /011 8 67 8089
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን