የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ስዲግ/ግጨO03/2013
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፁትን ኮንፈረንስ ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
|
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
|
1 |
ኮንፈረንስ ወንበር /conference chair/ |
በቁጥር
|
400 |
12,000.00
|
መስከረም 20 ቀን2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
|
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ ታክስ (VAT) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና የመንግስት ግዥ ንብረትና አስተዳደር አጀንሲ ተመዝጋቢ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ፒያሳ ደጎል አደባባይ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ዋናው መ/ቤት ፕሮክዩርመንት ሎጀስቲክስ ንብረት እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 204 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ማለትም መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በፕሮክዩርመንት ሎጀስቲክስ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 204 ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0111-560148 መደወል ይችላሉ፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት