የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-04/2012
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮተቤ ጋራዥ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የከባድና የቀላል ተሸከርካሪ ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ቁጥር
|
የዕቃው ዓይነት
|
የሚገኝበት ቦታ
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
|
የጨረታ መዝጊያ
|
የጨረታ መክፈቻ
|
1 |
የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የከባድና የቀላል ተሽከርካሪ ጐማዎች
|
ኮተቤ ጋራዥ
|
በቁጥር
|
5,460
|
32,112.85
|
ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓም ከቀኑ 8፡00
|
ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30
|
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወረቀት፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ፒያሳ ደጎል አደባባይ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ንብረት አስተዳር ቢሮ ቁጥር 415 በመምጣት ብር 400.00 (አራት መቶ) የማይመለስ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 415 ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 011-156-04-12 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት