ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ስዲግ–ግጨ002/2013
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች በውስን ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
|
1 |
ከአሽከርካሪው ጭምር 5 ሰው የሚጭን አውቶሞቢል መኪና |
በቁጥር
|
40 |
600,000.00
|
ነሃሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
ነሃሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
|
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ፒያሳ ደጎል አደባባይ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ዋናው መ/ቤት ፕሮክዩርመንት ሉጀስቲክስ ንብረት እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 204 የማይመለስ ብር 4000 /አራት ሺህ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰአት ነሃሴ15/2012 ዓም ድረስ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ማለትም ነሃሴ 15/2012ዓ.ም ከሰዓት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በፕሮክዩርመንት ሎጀስቲክስ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 204 ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 011-560148 መደወል ይችላሉ፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻላ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት