ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር /UEAP/BENISHANGUL GUMZ REG/NCB/02/13
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሪጅን ጽ/ቤት በአሶሳ ፣ በመተከል እና በካማሽ ዞን ከዕቃ ግምጃ ቤቶች ወደ ተለያዩ የገጠር ከተሞች፣ ቀበሌዎችና መንደሮች ዕቃ ለማጓጓዝ፣ የተለያዩ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ምሰሶዎች እንዲሁም የመስመር ሰራተኞችንና ሌሎች ተዛማጅ በትራንስፖርቴሽን/ስራዎች ለማከናወን 02/ሁለት/ መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዎችን ለአንድ ዓመት በኪራይ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- ተጫራቾች በዘርፉ ተሰማርተው ለመስራት ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያከናወኑበት እንዲሁም የተሽከርካሪዎች አጠቃላይና የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሪጅን ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለአንድ ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 አምስት ሺህ ብር/ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ለEEU-UEAT BENISHANG GUMz REGION CPO በማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ የጨረታ ቁጥር UEAP/ BENISHANGUL GUMZ REG/NCB/02/13 የሚል ምልከት በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 28 ቀን/2013 ዓ.ም 8.30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0577750979 ወይም 0577751083 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገር
አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጽ/ቤት /አሶሳ /