የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/PP/NCB/04/2013
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዋናው ዕቃ ግ/ቤት ግንባታ ግብዓት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት እና ሰዓት ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋናው መ/ቤት ፕሮኪዩርመንት ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከቱትን ዕቃዎች የዋጋ ዝርዝር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/PP/NCB/04/2013 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በሲፒኦ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መከፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
የተለያዩ ለግንባታ ግብዓት የሚውሉ የሕንፃ እና ኤሌክትሪክ ዕቃዎች |
50,000
|
ነሐሴ 18 ቀን 2012ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ነሐሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት
|
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 58 07 81/06 27 መደወል ይችላሉ ::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል